የሐራጅ ማስታወቂያ
Urgent

Tender Overview

Location
Addis Ababa, Addis Ababa
Tender Type
Auction
Bidding Date
2024-04-16
Documnt
Download
Date Posted
1 month ago

Additional Details

Tender ID
1462
Tender Views
111

Tender Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አቶ ኤልያስ ሴባ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ እታገኝ እሸቴ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 108267 በ6/2/2016 ዓ.ም እና በመ/ቁ 1837 በ15/4/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 8 ይዞታው መለያ ቁጥር AA000070803980 የፍ/ባለዕዳ ስም የተመዘገበ የቦታው ስፋት 90 ካ/ሜ ሲሆን የቤቱ ስፋት 67.72 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 5,269,260 (አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 8 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል

ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመወሰድ መጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም C.RO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ5 ቀን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።

የፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Similar Tenders

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Urgent

Auction

ዳሸን ባንክ አ.ማ

የሐራጅ ማስታወቂያ
Urgent

Sale

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

የሠ/ቁ/ኮድ-2-B--83248 አ.አ የሆነው /ሀይሉክስ/ ሐራጅ ሽያጭ
Urgent

Auction

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

721 /ሰባት መቶ ሃያ አንድ አክሲዮን ሽያጭ ጨረታ
Urgent

Auction

Cookies

This website uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Accept